ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አልብሪክ ባህላዊ የውኃ ማቀዝቀዣ በዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት (ብራንድ) እንዲመዘገብ ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀርባል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አልብሪክ ባህላዊ የውኃ ማቀዝቀዣ በዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት (ብራንድ) እንዲመዘገብ ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋና ያቀርባል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካሉት በርካታ ባህላዊ የዕደ ጥበብ ውጤቶች መካከል ባህላዊ የውኃ ማቀዝቀዣ የሆነው አልብሪክ አንዱ ነው።

የቤኒሻንጉል ብሔረሰብ ባህላዊ የውሀ ማቀዝቀዣ የሆነው አልብሪክ በአሠራር ጥበቡ ብቻ ሳይሆን ውኃን የሚያቀዘቅዝበት መንገድ አስደናቂ ነው።

ባለፉት ጊዜያት ምርቱን በዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል።

ይህ ጥረት ተሳክቶ ባህላዊ የውኃ ማቀዝቀዣ የሆነው-አልብሪክ የእደ ጥበብ ውጤት በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ምዝገባ የምስክር ወረቀት በማግኘቱ ለመላው የክልሉ ሕዝብ እንኳን ደስ አላችሁ።

ባህላዊ የውሀ ማቀዝቀዣ የሆነው አልብሪክ የእደ ጥበብ ውጤት በኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በኩል በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ሆኖ እንዲመዘገብ የኢ.ፌ.ድ.ሪ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ባደረጉት ጥረት አልብሪክ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የንግድ ምልክት ምዝገባ የምስክር ወረቀት አግኝቷል፡፡

በዚህም አልብሪክ ባህላዊ የውኃ ማቀዝቀዣ በኢትየጵያ በንግድ ምልክትነት ከተመዘገቡ ባህላዊ ምርቶች ሶስተኛው መሆን ችሏል። ይህም ምርቱን በይበልጥ ለማስተዋወቅ ካለው ፋይዳ ባሻገር ምርቱን ከፈጠራ መብት ስርቆት ለመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

ባህላዊ ምርቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት (ብራንድ) መመዝገቡ ለመላው የክልሉ ሕዝብ ታላቅ ኩራት ነው።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አልብሪክ በዓለም አቀፍ የንግድ ምልክት (ብራንድ) መመዝገቡ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው በመሆኑ፣ ይህ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የላቀ ምስጋና ያቀርባል።

ለመላው የክልሉ ሕዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ታህሳስ፣ 24/2016 ዓ.ም

አሶሳ፣

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *