በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሩዝ ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ ነው፦ አቶ አሻድሊ ሀሰን

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሩዝ ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

‎ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን በባምባሲ ወረዳ በ90 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ የሚኘውን የሩዝ ክላስተር ጎብኝተዋል።

‎አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ጠቁመው፣ በዚህም በተያዘው የምርት ዘመን የተሻለ ውጤት ይጠበቃል ብለዋል።

የሩዝ ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፣ በባምባሲ ወረዳ በክላስተር እየለማ የሚገኘው ሩዝ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አቶ አሻድሊ ተናግረዋል።

‎ክልሉ ለግብርናው ዘርፍ ምቹ የሆነ አቅም እንዳለው የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ይህንን አቅም በመጠቀም በመኸር እርሻ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በተረጂነት ቅነሳ አበረታች ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *