
(አሶሳ፣ መስከረም 22/2018 ዓ/ም) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እውን ለማድረግ የመንግስት ሰራተኞች በጋራ መቆም እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ ገለጹ።
”የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት” በሚል ወቅታዊና ሀገራዊ ሰነድ ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክር ቤት ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አስካለች አልቦሮ እንደገለጹት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያጋጥሟትን ውስጧዊና ውጫዊ ፈተናዎችን በመሻገር አመርቂ ውጤቶች እያስመዘገበች እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የመንግስት ሰራተኛው አንድነቱን ሊያማጠናከር ይገባል ብለዋል።

የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ “የታደሰ ጂኦ-ስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!” የሚል ሰነድ ባቀረበቡት ወቅት እንደገለጹት መንግስት ሰራተኞች ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ሁኔታዎች በአግባቡ መረዳት እንዳለበት ገልጸዋል።
ፈተናዎች ድሎችን እንድንቀናጅ በር እየከፈተ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊያን አንድነታቸውን በፅኑ መሰረት ላይ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።
ጠንካራ ሀገር ለመፍጠር ሲቪል ሰርቫንቱ የአገልጋይነት ስሜትን በመላበስ የተገልጋዮችን እርካታ ማሳደግ ተቀዳሚ አጀንዳው ማድረግ እንደሚጠበቅበትም ተናግረዋል።
ያለፉትን ኩስመና አጀንዳ በመዝጋት ወደ ሀገራዊ ዘላቂ ቁመና ለመሸጋገር የጋራ ርብርብ እንደሚጠይቅም አቶ መለሰ ገልጸዋል።

በመድረኩም የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት፣ የክልሉ ምክር ቤት፣ የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ የክልሉ ዋና ኦዲተር መ/ቤት፣ የታላቁ ህደሴ ግድብ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽ/ቤት፣ የክልሉ ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጄንስ አመራሮችና ሰራተኞች ተገኝተዋል።
