የአሶሳ ከተማ አስፓልት መንገድ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው፡፡አቶ አበራ ባዬታ

በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ከተማ አስፓልት መንገድ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የመሰረተ ልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አማካሪ አቶ አበራ ባዬታ ተናገሩ፡፡

የአሶሳ ከተማ የአስፓልት መንገድ ግንባታ ለማከናወን የአስፓልት ማሽን ተከላ በማጠናቀቅ 19.7 ኪ.ሜትር የሚሸፍን እና በተያዘው በጀት ዓመት 6.9 ኪ.ሜትር ጥራቱን የጠበቀ አንደኛ ደረጃ ኮንክሪት የአስፓልት ንጣፍ ስራን ለማከናወን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በትኩረት እየተከታተሉት መሆኑን አቶ አበራ ተናግረዋል፡፡

የአሶሳ ከተማ አስፓልት ክሮስ ላንድ/cross land/ በሚባል ተቋራጭ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት አቶ አበራ አጠቃላይ የመንገዱ ግንባታ ወጪውም 1.15 ቢሊዮን/አንድ ነጥብ አንድ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ እና የአስፓልቱ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅም የክልሉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ከማነቃቃት በተጨማሪ ውብ እና ማራኪ ከተማ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የተቋራጭ የኤሌክትሮ መካኒካል ባለሙያ አቶ ተክለሀይማኖት አክልሌብርሀን በበኩላቸው ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቅ የአስፓልት ማሽነሪ ተከላውን በማጠናቀቅ ወደ ምርት ማምረት ስራው ለመግባት አስፈላጊውን ዝግጅት መጨረሳቸውንና የትራንስፎርሜር ተከላ ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ያነጋገርናቸው የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው የመንገዱ ግንባታ ያለበት ሂደት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረው ግንባታው ሲጠናቀቅ ይደርስባቸው የነበረው እንግልት እና አቧራን እንደሚያስቀርላቸው ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ትክክለኛ የመረጃ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ

ፌስቡክ (Facebook)፡- https://www.facebook.com/bgrscomoffice

ቴሌግራም (Telegeram)፡- https://t.me/BGRSGCOMMUNICATIONBEAROU

ዌብሳይት (Websit) www.bgrsgcab.gov.et

ቲውተር (Tiwtter)፡- https://twitter.com/bgrsgcab

One thought on “የአሶሳ ከተማ አስፓልት መንገድ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው፡፡አቶ አበራ ባዬታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *