ቢሮዉ በአዋጅ ከተሰጡትና ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከልም ዋና ዋናዎቹ

የተለያዩ ወቅታዊ መረጃዎችን ከመንግስት ወደሕዝብ እንዲሁም ከሕዝብ ወደ መንግስት በማድረስ እንደ ድልድይ ሆኖ የቃል አቀባይነት ሚናውን እየተወጣ ይገኛል፡፡

ሃገራዊና ኃይማኖታዊ በዓላትን እንዲሁም ክልላዊ መድረኮችን በውጤታማነት ይመራል፡፡

ክልላዊና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዲሁም በተሳሳተ መንገድ ስለክልሉ የሚሠራጩ መረጃዎችን በተመለከተ የመንግስትን አቋም የሚገልጽ መግለጫ በማዘጋጀት በጽ/ቤቱ ማኅበራዊ ሚዲያ እንዲሁም በክልሉ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ለህብረተሰቡ ያደርሳል፡፡

ህብረተሰቡን ከከፍተኛ አመራሩ ጋር በማገናኘት በማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና መልካም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይቶችን ያዘጋጃል፡፡

ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመነጋገር ማብራሪያ በሚያስፈልጋቸው የክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለሚዲያ አካላት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጥ ያስተባብራል፡፡

በተለያዩ ወቅታዊ ሃገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሕዝብ አስተያት ዳሰሳ ጥናት ያካሂዳል፤ ጥናቱን ይተነትናል፤ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ግብዓት ግብዓት ያቀርባል፡፡

ሕብረተሰቡ በየአካባቢው መራጃዎችን የሚያገኝባቸውን አነስተኛ ሚዲያዎች (ቲቪ ፓርክ፣ የማስታወቂያ ሠሌዳ፣ ሚኒ ሚዲያ፣ የመረጃ ማዕከላት…) እንዲደራጁ ያስተባብራል፣ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡

ከክልሉ ሁሉም ወረዳዎች መረጃዎችን በማሰባሰብ ሳምንታዊ መረጃን በየዘርፉ በማደራጀት ለክልሉ መንግስት ግብዓት ያቀርባል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተሰጠ ያለው "ከዕዳ ወደምንዳ" የአቅም ግንባታ ስልጠና ወቅቱ የሚፈልገውን የአመራር አቅም ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን የክልሉ ኮሚንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሓይ ሞርካ ገለጹ::

ስልጠናው አመራሩ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተገንዝቦ፣ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፣ ሀገራቱ የጀመረችውን ዕድገት ከዳር ለማድረስ የሚያስችል አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ወ/ሮ ፀሓይ ሞርካ ተናግረዋል።በክልሉ ለአመራሩ እና ለአባላት እየተሰጠ ባለው የአቅም ግንባታ ስልጠና ሀገራዊ ገዥ ትርክት እሳቤን በማስረፅ የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ከዳር ማድረስ ያስፈልጋል ብለዋል።ያሉንን ሀብቶች በአግባቡ በመጠቀም ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ያሉት ወ/ሮ ፀሓይ ሞርካ፣ የፓርቲው አመራሮች እና አባላቱ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና ልማቱን ለማፋጠን የሚስችል አቅም ከስልጠናው እንደሚያገኙም ገልጸዋል፡፡የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ማምጣት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮችን እና አባላት በስልጠና አቅም የመገንባት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።እንደ ወ/ሮ ፀሓይ ሞርካ ገለፃ፣ ምሁራንን ጨምሮ በክልሉ ከ68ሺ በላይ የሚሆኑ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችንና አባላት ስልጠናውን እንደሚወስዱም ተናግረዋል።ስልጠናውም በሁሉም ማዕከላት ለተከታታይ 4 ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ እንደሚሰጥም ተገልጿል።

አድራሻ