በክልሉ በመንግስት በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እንዲገነቡ ጥብቅ ክትትል ይደረጋል።”አቶ አሻዲሊ ሀሰን
**,,
(አሶሳ፣ታህሳስ 26/2016 ዓ/ም በክልሉ በመንግስት በጀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እና በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እንዲገነቡ እና እንዲጠናቀቁ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ተናገሩ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን የተመራው ልዑክ በአሶሳ ከተማ እየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
በመንግስት እና በህዝብ ውስን ሀብት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ጥራታቸውን ጠብቀው እና በተያዘላቸው የጊዜ ሰለዳ ተጠናቀው ለማህበረሰቡ አገለግሎት እንዲሰጡ ጥብቅ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝ ርዕሰ መስተዳድር አሻዲሊ ሀሰን ተናግረዋል።
መንግስት በመፍጠን እና በመፍጠር ሂደት ውስጥ እያከናወናቸው ያሉ ፕሮጀክቶች በተያዘው ጊዜ ተጠናቀው የማህበረሰቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል።
ዛሬ ላይ የሚሰሩ ታላላቅ ፕሮጀክቶች የአጭር ጊዜ አገልግሎት ሳይሆን ዘመን ተሻጋሪ እና ለመጪው ትውልድ የምናስተላልፈው ቅርስ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።
እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ከማድረግ በተጨማሪ በተያዘው ዲዛይንም መሠራቱንም ከተቋራጭ ድርጅቶች እና አማካሪ ድርጅቶች ጋር በቅርበት ይሰራል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በጉብኝቱም በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘው ገንዘብ እየተገነባ የሚገኘው ዘመናዊ ሙዚዬም፣በክልሉ ስራ አመራር እየተሰራ የሚገኘው ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና የሰልጣኞች ማደሪያ ክፍሎችም ይገኙበታል።