ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ ገለጹ።
የቢሮው ማኔጀመንት የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት መደበኛ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ገምግሟል።
የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ፣ ቢሮው ሃገራዊ እና ክልላዊ ሁነቶችን በበላይነት በመምራትና በማስተበበር የላቀ ሚና መጫወቱን ገልጸዋል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራዎች ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው ለማስቻልም በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ተቋማት በተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ አውታሮች የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ማድረግ መቻሉን አቶ መለሰ ተናግረዋል።
በተለይም በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ሁሉን አቀፍ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ጎልተው እንዲወጡ በማድረግ ወቅታዊና ታዓማኒነት ያላቸው መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ ስለመቻሉ ኃላፊው ጠቁመዋል።
ተቋሙ በክልሉ ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ በመሆን የክልሉን ህብረተሰብ የመረጃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የተጀመሩ ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባው አቶ መለሰ አስገንዝበዋል።
የቢሮው ማንጅመንት አባላት በበኩላቸው፣ በተግባቦት ስራዎች ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ አጉልቶ በማስቀጠል በአፈጻጸም ወቅት የተለዩ ውስንነቶችን በቀሪ ወራት የእቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሰሩም ነው የገለጹት።