ባለፉት የለውጥ ዓመታት አርሶ አደሩን የግብርና መካናይዜሽን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን ተጠቃሚ እንዲሆን በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን ተናገሩ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ 8ኛ ዙር የግብርና ልማት አማካሪ ካውንስል ጉባኤ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፤የክልሉን አርሶ አደር ህይወት ለመቀየር እና ከባህላዊ የአስተራረስ ዘዴዎች በማላቀቅ የአርሶ ደሩን ምርት እና ምርታማነት ለማሳደግ በርካታ ተግባራት መከናወን መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት የለውጥ ዓመታት አርሶ አደሩ የግብርና መካናይዜሽን ተጠቃሚ ለማድረግ በተሰራው ስራ አመርቂ ውጤት መመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አውስተዋል፡፡

የግብርና ስርዓትን በማዘመን የኢኮኖሚ ሽግግር መፍጠርም ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድር አሻዲሊ ሀሰን ፤የአርሶ አደሩን ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ በየደረጃ የሚገኙት ባለድርሻ አካላት በአትኩሮት ሊሰሩበት ይገባል ብለዋል፡፡

በየአካባቢው የሚገኙ አነስተኛ የመስኖ ግድብ ግንባታዎችን አርሶ አደሩ እንዲጠቀም በማድረግ ከዝናብ ጠባቂነት በማላቀቅ የኑሮ ውድነትን ከመቀነስ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን የበለጠ ማጉላት ይጠይቃል ፡፡

በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት ተቋማት እና ምርምር ተቋማት አዳዲስ የምርምር ውጤቶች ለአርሶ አደሩ በማቅረብ ረገድ አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

የግብርና ስራ የተቀናጀ የህዝብ ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ ከማሳ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ምርት ድረስ ያለውን ሂደት የግብርና ባለሙያዎች ውጤታማ የሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኻልፋ ፤የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል፡፡

ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመፍጠር በየዓመቱ የሚሰሩ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎች ከሰው እና ከእንስሳት ንኪኪ ነፃ ማድርግ እንደሚገባም ተናረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *