አትሌት ፅጌ ዱጉማ ለሌሎች ታዳጊዎች ተምሳሌት እንደምትሆን የካማሽ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
አትሌት ፅጌ ዱጉማ በስኮትላንድ ግላስኮው በተካሄደው የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ወርቅ በማስገኘት እና በዓለም መድረክ የሀገሯን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
አትሌቷ ያስመዘገበችው ድል ለሌሎች ታዳጊዎች መነሳሳትን የሚፈጥር እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎቹ ገልፀዋል።
ክልሉ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ሀገርን የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ማፍራት ይችላል የሚሉት የከተማዋ ነዋሪዎች የማሰልጠኛ ማዕከላትን ማቋቋም ፕሮጀክቶችን ማጠናከር እና መደገፍ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ፅጌ ዱጉማን ከታዳጊነት ጊዜዋ ጀምሮ የሚያውቃት የካማሽ ዞን የስፖርት ሳይንስ ባለሙያው ታከለ ደባልቄ በዞን እና በክልል ውድድሮች ላይ አሸናፊ የነበረች ልጅ እንደሆነች መግለጻቸውን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሚዲያ ዘግቧል።