የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ የሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ9ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የግምገማ መድረክ በአሶሳ ከተማ መካሄድ ተጀመሯል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፤ፓርቲው የክልሉን ነባራዊ ሁኔታዎችን እና አዝማሚያዎችን በመለየት የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት ማከናወን መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው መላውን ህዝብ እና አባሉን በማሳተፍ በክልሉ የተገኘውን አንፃራዊ ሠላም በመጠቀም ህዝቡ በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤በየደረጃው የተለያዩ ህዝባዊ ኮንፍረንሶችን በማድረግ የተጠናከረ የህዝብ ግንኙነት ስራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአቅም ግንባታ እና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት የሚነሱበትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ተግዳሮቶችን በመቋቋም ዛሬ ላይ የሚታያውን ወጥነት ያለው ፓርቲ መመስረት መቻሉን አውስተዋል፡፡
በመላ ሀገሪቱ ተፈጥሮ የነበረውን የፀጥታ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ መፍታት ተችሏል ያሉት ዶ/ር ሰማ ጥሩነህ ፤ከለውጡ ማግስት የነበረውን የፖለቲካ ስርዓት በመለወጥ ምቹ የፖለቲካ ምህዳር መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በዚህ የግምገማ መድረክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተገኙ ድሎችን በማስቀጠል እና በውስንነቶች ላይ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የግምገማ መድረኩም ለተከታታይ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከወጣው መረሃ ግብር መረዳት ተችሏል፡፡


