በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አባላት ክልላዊ ማጠቃለያ ኮንፍረንስ “ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው።
በኮንፍረንሱ ላይም ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት አምስት ዓመት የምርጫ ዘመን የሁለት ዓመት ተኩል አፈጻጸም ፣ተግዳሮቶች እና የተገኙ ውጤቶች በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኮንፍረንሱ ማጠቃለያ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻዲሊ ሀሰን፣የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፤ የክልሉ ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር፣ የክልሉ ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስን ጨምሮ የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣በየደረጃው የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ አባላት እየተሳተፉበት ይገኛል፡፡
